District of Columbia Office of Human Rights

08/21/2026 | Press release | Distributed by Public on 08/21/2026 09:33

የ ዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ( OHR ) የኦገስት 2026 ወርሃዊ የዜና መጽሔት - የዳይሬክተሩ መዕክት (Amharic)

ዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ( OHR ) የኦገስት 2026 ወርሃዊ የዜና መጽሔት - የዳይሬክተሩ መዕክት

የተከበራችሁ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች፦

የበ /ሰመር/ ወቅት እየተጠናቀቀ ሲመጣ የገነባናቸውን ግንኙነቶች፣ ያከበርናቸውን ማህበረሰቦች እና እያንዳንዱ ሰው በክብር፣ በፍትሃዊነት እና በእኩልነት መታየቱን ለማረጋገጥ ሁላችንም ያለብንን የጋራ ኃላፊነት የምናስብበት ጊዜ ነው። የሲቪል መብቶችን መጠበቅ አድልዎ ምክንያት ለሚደርስ በደል ምላሽ ከመስጠት ያለፈ ትርጉም ነው ለው። በተጨማሪም እያንዳንዱ ሰው በዲስትሪክቱ ውስጥ በማኅበራዊ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የመሳተፍ እድል እንዳለው ለማረጋገጥ ከነዋሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንግዱ ተቋማት ፣ የማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ከመንግሥት አጋሮቻችን ጋር አብሮ መሥራትንም ያመለክታል። ሰዎች መብቶቻቸውን እና ኃላፊነቶቻቸውን እንዲረዱ በማገዝ እና የዲስትሪክቱን ህግ ማከበርን በመደገፍማኅበረሰቦቻችንን እናጠናክራለን፣ እንዲሁም ለሁሉም ሰው እኩል እድል መኖሩን እናረጋግጣለን። በበጋው ወቅት በሙሉ፣ ለተደራሽነት፣ ለአካታችነት እና ለእኩል እድል ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት እያደስን፣ ዋሽንግተን ዲሲን የበለጠ ጠንካራ የሚያደርጉትን የተለያዩ ማኅበረሰቦችን ስናከብር ቆይተናል።

ለዚህ ቁርጠኝነት እንደ አንድ ምሳሌ የሚጠቀሰው Access to Expression (ሀሳብ የመግለጽ እድል)፦ የአሜሪካ አካል ጉዳተኞች መብት አዋጅ (ADA) 36ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ለማክበር የተዘጋጀው Celebrating Inclusive Arts in the District (በዲስትሪክቱ ውስጥ አካታች ጥበባትን ማክበር)። ( የማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ ማጠቃለያችንን ለማየት እዚህ ይጫኑ። ) ከ የአካል ጉዳተኞች መብት ቢሮ ከዲሲ የእድገት እክል ምክር ቤት፣ ዲሲ የጥበብ እና የሰብአዊነት ኮሚሽን ፣ ከ ዲሲ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት እና ከ Art Enables ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ዝግጅት፣ ተደራሽነት የባህል ተቋሞቻችንን እንዴት እንደሚያጠናክር እና አካል ጉዳተኛ የሆኑ አርቲስቶች በማኅበረሰብ ሕይወት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የመሳተፍ እድል እንደሚፈጥር አጉልቶ አሳይቷል። በጥበብ፣ በውይይት እና በጋራ ልምምዶች ነዋሪዎችን ማቀራረብ የ ADAን ዘላቂ ውርስ የሚያንፀባርቅ ሲሆን እያንዳንዱ ሰው አስተዋፅኦ የሚያደርግበት እና የባለቤትነት ስሜት የሚሰማውን ዲስትሪክት የመገንባት የጋራ ኃላፊነታችንንም አጠናክሮታል።

ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ስንዘጋጅ ተመሳሳይ የሆነ ለአካታችነት ያለው ቁርጠኝነት ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች እና ለመምህራን በተለየ ሁኔታ አስፈላጊ ሆኖ ይቀጥላል። እያንዳንዱ ተማሪ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ የተከበረ እና የተደገፈ እንደሆነ በሚሰማው አካባቢ የመማር መብት አለው። በ OHR የወጣቶች ትንኮሳ (Bullying) መከላከል ፕሮግራም (YBPP) በኩል፣ ትንኮሳን ለመከላከል፣ የዲስትሪክቱን ሕግ ማከበርን ለማጠናከር፣ እና ለመምህራን፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ደኅንነቱ የተጠበቀ እና አካታች የመማሪያ አካባቢዎችን ለመፍጠር የሚያስፈልጉትን ግብአቶች ለማቅረብ ከትምህርት ቤቶች እና ወጣቶችን ከሚያገለግሉ ድርጅቶች ጋር በንቃት እንሠራለን። ጥቂት ዋና ዋና ነጥቦች የሚያካትቱት ትንኮሳ ማንነትዎ ላይ ሲያነጣጥር፦ ለ LGBTQIA+ ወጣቶች ፈጣን መመሪያ ፣ የእኛ የሳይበር ትንኮሳ ምክሮች ወረቀት ፣ እና መታተም የሚችል የወጣቶች ትንኮሳ መከላከል ፖስተር ናቸው።

በዚህ የበ ጋ/ሰመር/ ወቅት፣ YBPP ከሆርተን ሕፃናት እና ብሔራዊ የሕፃናት እና ቤተሰቦች ማዕከል (Horton's Kids and the National Center for Children and Families) ጋር በመተባበር ለአንደኛ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስምንት ወርክሾፖችን አዘጋጅቷል። በጋራ፣ ወጣቶች በትምህርት ቤቶቻቸው እና በማኅበረሰቦቻቸው ውስጥ ደግነትን፣ አካታችነትን እና እርስ በርስ መከባበርን የሚያበረታቱበትን፣ እንዲሁም ትንኮሳን ለይቶ ለማወቅ፣ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የሚረዱ ተግባራዊ ክኅሎቶችን እንዲያግኙ ረድተናል።

ይህ ሥራ በትምህርት ዘመኑ በሙሉ ይቀጥላል። ትምህርት ቤቶች እና ወጣቶችን የሚያገለግሉ ድርጅቶች የዲስትሪክቱን ሕግ ማከበር የሚደግፉ እና ለእያንዳንዱ ተማሪ ተስማሚ የመማሪያ አካባቢዎችን ለመፍጠር የሚረዱ ቴክኒካዊ ድጋፎችን፣ የትምህርት ግብአቶችን፣ ምሳሌ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን ማግኘት ይችላሉ። ቤተሰቦች፣ መምህራን እና የማኅበረሰብ አባላት ያሉትን ግብአቶች እና ድጋፎች የበለጠ ለማወቅ የወጣቶች ትንኮሳ መከላከል ፕሮግራም (Youth Bullying Prevention Program) ድሕረ ገጽን እንዲጎበኙ እናበረታታለን።

የሲቪል መብቶችን መጠበቅ የጋራ ኃላፊነት ነው። ወደፊት ስንጓዝ እድሎችን ለማስፋት፣ እምነትን ለማጠናከር እና እያንዳንዱ ሰው ከእኩልነት መጓደልና ከአድልዎ ነፃ ሆኖ መኖር፣ መሥራት፣ መማር እና ማደግ እንደሚችል ለማረጋገጥ ከነዋሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ንግዱ ማህበረሰብ ክፍሎች ፣ የማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ከመንግሥት አጋሮቻችን ጋር አብሮ ለመሥራት ቁርጠኝነታችን ይቀጥላል። በአንድነት፣ ለሁሉም ሰው የበለጠ አካታች፣ አካታችና ፍትሃዊ ዲስትሪክት መገንባታችንን መቀጠል እንችላ ለን።

District of Columbia Office of Human Rights published this content on August 21, 2026, and is solely responsible for the information contained herein. Distributed via Public Technologies (PUBT), unedited and unaltered, on August 21, 2026 at 15:34 UTC. If you believe the information included in the content is inaccurate or outdated and requires editing or removal, please contact us at [email protected]